Cover of በወላይታ ዞን የተካሄደውን የድጋሚ ሕዝበ ውሳኔ  የመራጮች ምዝገባ እና የድምጽ አሰጣጥ ሂደትን  አስመልክቶ የመጀመሪያ ደረጃ የትዝብት ሪፖርት
Observation reports

በወላይታ ዞን የተካሄደውን የድጋሚ ሕዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ እና የድምጽ አሰጣጥ ሂደትን አስመልክቶ የመጀመሪያ ደረጃ የትዝብት ሪፖርት

Published
June 29, 2023
Type
Observation reports
Language
Amharic
Format
PDF
Size
13.2 MB
Downloads
932
Views
8
Share Telegram Facebook X WhatsApp Email

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ውስጥ የሚገኙ ከ10 የሚበልጡ ዞኖች ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ የራሳቸውን ክልላዊ መንግሥት ለመመስረት ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወቃል። በዚህም መሰረት በሕዳር 2011 ዓ.ም እና በመስከረም 2014 ዓ.ም ከተካሄዱ የሕዝበ ውሳኔዎች በኋላ የሲዳማ ክልል እና የደቡብ ምዕራብ ክልሎች ተመስርተዋል።

በተመሳሳይ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ስር የሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች አዲስ ክልል እንዲመሰረት በየምክር ቤቶቻቸው አማካኝነት ውሳኔ አሳልፈዋል። በዚህም መሰረት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስማቸው ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ሕዝበ-ውሳኔ እንዲያደራጅ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መመሪያ ሰጥቷል። የምርጫ ቦርድም ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በስድስቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ እና ጎፋ) እና በደቡብ ክልል አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ እና ደራሼ) ሕዝበ ውሳኔ ማካሄዱ ይታወሳል። ኅብረት ለምርጫም በስድስቱ ዞኖችና በአምስቱ ልዩ ወረዳዎች 434 ተቀማጭ እና 76 ተንቀሳቃሽ ታዛቢዎችን መልምሎ በማሰልጠን ለትዝብት አሰማርቷል። ነገርግን የምርጫ ቦርድ በመራጮች ምዝገባ እና በድምጽ አሰጣጥ ሂደት ከፍተኛ የሆነ የህግ ጥሰት መፈፀሙን በመጥቀስ በወላይታ ዞን የተካሄደውን ሕዝበ ውሳኔ ውጤት ሰርዟል። ይህንንም ተከትሎ የምርጫ ቦርድ በወላይታ ዞን ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. የሕዝበ ውሳኔው በድጋሚ እንደሚካሄድ ለባለድርሻ አካላት አስታውቋል። በዚህም መሰረት ኅብረት ለምርጫ ለወላይታ ዞን አዋሳኝ በሆኑ ዞኖች የሚገኙ ስድስት አባል ድርጅቶቹን በማሳተፍ 190 ታዛቢዎችን መልምሎ፤ ከመካከላቸው በአጠቃላይ 146 (118 ተቀማጭ እና 28 ተንቀሳቃሽ) ታዛቢዎችን አሰማርቶ የመራጮች ምዝገባ እና የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን በመታዘብ  ይህንን የመጀመሪያ ደረጃ የትዝብት ሪፖርት አዘጋጅቷል።