የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ (ኅብረት ለምርጫ) 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ትዝብት ግኝቶችን በተመለከተ የተዘጋጀ ረፖርት

 

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ (ኅብረት ለምርጫ)፣ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባገኘው የትዝብት ፈቃድ፣ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በመታዘብ ላይ ይገኛል። ኅብረቱ የመራጮች ምዝገባ ሂደትን የሚታዘቡ 522 የረዥም ጊዜ ታዛቢዎችን ከትግራይ ክልል እና አከራካሪ ከሆኑ ቦታዎች በስተቀር በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች እና የከተማ መስተዳደሮች አሰማርቶ ሲታዘብ ቆይቷል።

ይህ ሪፖርት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በማኑዋል(manual) እና በታብሌት በመታገዝ ያካሄደውን የመራጮች ምዝገባ ሂደት ኅብረት ለምርጫ ስልታዊ (Systematic) በሆነ መንገድ ፤ ወጥነት ያላቸውን የትዝብት ቅጾች (Checklists) በመጠቀም በተመረጡ አመላካቾች (Key indicators) መዝኗል። ይህ ሪፖርት በዋነኝነት የመራጮች የምዝገባ ሂደት፤ የሂደቱን አካታችነት (ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን እና አቅመ ደካሞችን ማሳተፉ)፤ በምዝገባ ጣቢያዎች አካባቢ የነበረው የጸጥታ አስከባሪዎች ስምሪት እና የምርጫ ደህንነትን ዳስሷል። 

ሪፖርቱ ከመጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ምዝገባው እስከተጠናቀቀበት ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ያለውን የመራጮች ምዝገባ ሂደት የሚሸፍን ሲሆን ኅብረት ለምርጫ 522 የረዥም ጊዜ ታዛቢዎችን ባሰማራባቸው 3,953 የማኑዋል እና 443 የታብሌት በአጠቃላይ ከ4,396 የምዝገባ ጣቢያዎች በተሰበሰቡ ግኝቶች ላይ የተመሰረት ነው። 

በዚህ ሪፖርት የቀረቡት ማንኛውም በመቶኛ (%) የተቀመጡ ግኝቶች ኅብረቱ ከታዘባቸው 3,953 የማኑዋል እና 443 የታብሌት የምዝገባ ጣቢያዎች አኳያ የተሰሉ ናቸው

1 file
pdf
የመራጮች ምዝገባ ትዝብት ሪፖርት--.pdf
1.5 MB