መግቢያ
በኢትዮጵያ የረጅም ዘመናት ታሪክ ውስጥ ፤ በተለያየ ዘርፍ እና በተለያየ መንገድ ሴት ኢትዮጵያዊያን ለሀገራቸው ያበረከቱት አስተዋዕፆ ተፅፎ እና ተሰንዶ ሊቀመጥ ከሚችለው በላይ ሰፊ እና መልከ ብዙ ነው። እነዚህ ሴቶች ቤታቸውን ከማቆም ጀምሮ በሀገር መሪነት ፤ በፖለቲካ ፤ በህክምና ፤ በሳይንስ፣ ኪነጥበብ እና ማህበራዊ አንቂነት የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ለህብረተሰባቸው እና ለሃገራቸው ከፍተኛ አስተዋጾዖ አበርክተዋል። ለመጪው ትውልድም ፈር በመቅደድ አራአያ መሆን ችለዋል።
ይህ ኢንሳይክሎፔዲያ በተለያዩ ዘርፎች አርአያ መሆን የቻሉ ሴቶችን ታሪክ ይዟል። ብዙውን ጊዜ በባህላዊ የሥርዓተ-ፆታ ሚናዎች ተለይቶ በሚታወቅ ማህበረሰብ ውስጥ፣ እነዚህ አበረታች ሴቶች እንደ መሪ፣ አዲስ ነገር ጀማሪ እና የመብት ተሟጋች ሆነው ብቅ አሉ፣ ጽናትን እና ቆራጥነትንም አሳዩን። የእነዚህን አራአያ ሴቶች አብርክቶዋቸውን በመዘከር ሌሎች ሴቶች ራሳቸውን አብቅተው እውቀት እና ችሎታችውን ለህበረተሰባቸው ትርጉም ያለው አስተዋጻኦ አንዲያደርጉ የማነሳሳት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ፅኑ እምነት አለን ።
File | Action |
---|---|
አርአያ_V1.pdf | Download |