የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ (ኅብረት ለምርጫ) ከ175 በላይ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበራትን ያቀፈ ኅብረት ነው። ኅብረቱ ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ እና ገለልተኛ የሆነ የዜጎች የምርጫ ታዛቢ ቡድን ሲሆን ዋና ዓላማውም በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉን አቀፍ፣ ግልጽ እና በተጠያቂነት ምርጫዎች እንዲከናወኑ አስተዋጽኦ ማድረግ ነው።
በ2010 ዓም የተጀመረው የፖለቲካ ማሻሻያ ሂደት የተለያዩ የህግ እና ተቋማዊ ማሻሻያዎችን አድርጓል። ከተካሄዱት ማሻሻያዎች መካከል ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት የምርጫ ሕጉን ማሻሻል፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን እንደገና ማቋቋም፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ ሥርዓትን መከለስ እና አጠቃላይ የምርጫ ሁኔታን ማሻሻል ይገኙበታል። ምንም እንኳ እነዚህ ማሻሻያዎች ቢደረጉም በትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች የዴሞክራሲ ተሃድሶው ሂደቱን የሚያውኩ ብቻ ሳይሆን ክላይ በተዘረዘሩት ከለሎች በ2013 ዓም በተካሄደውአጠቃላይ ምርጫ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድሩ አፋሳሸ ግጭቶች ተከስተዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ምርጫ ቦርድ በቀድሞው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል እና የሶማሌ ክልል አንዳንድ የምርጫ ክልሎች በምርጫ ሂደቱ ላይ በታዩ ከፍተኛ ጉድለቶች ምክንያት የምርጫ ውጤቱን ሰርዟል። በዚህም ምክንያት የተወሰኑ የፌደራል ፓርላማ እና የክልል ምከር ቤቶች መቀመጫዎች ክፍት ሆነው ቆይተዋል።
ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ባልተከናወነባቸው አካባቢዎች እና ድጋሚ ምርጫ እንዲከናወንባቸው በቦርዱ ውሳኔ በተሰጠባቸው የምርጫ ክልሎች በተለይም በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ እፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ምርጫን ማድራጅት አስፈላጊ በመሆኑ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫዎችን በአራቱ ክልሎች እንደሚያከናውን ማሳወቁ እና ፤በመጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ቦርዱ የቀሪ እና ድጋሚ ምርጫዎች የሚካሄዱበትን የምርጫ የጊዜ ሠሌዳ ለህዝብ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በዚህ የጊዜ ሠሌዳ መሰረት ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም የድምጽ መስጫ ቀን እንዲሆን ተወስኖ የነበረ ቢሆንም ቦርዱ የምርጫው ቀን ወደ ሰኔ 09 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲተላለፍ አድርጓል። ነገር ግን ሰኔ 09 ቀን 2016 ዓ.ም ከዋለው የኢድ አል አድሃ ኃይማኖታዊ ክብረ በዓል ጋር በመገጣጠሙ ቦርዱ የድምጽ መስጫ ቀኑን በድጋሚ ወደ ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም አዘዋውሮታል። ከምርጫ ቦርድ በተገኘው መረጃ ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚካሄዱት ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫዎች በአጠቃላይ 1258 የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች (ከነዚህ ውስጥ 578 በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ 388 በአፋር፣ 123 በሶማሌ እንዲሁም 169 የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች እንደሚያቋቁም ገልጿል።
የትዝብት ግኝቶች አጭር ማጠቃልያ
ሰኔ 16 ቀን 2024 የተካሄደውን ቀሪ ምርጫ እና ድጋሚ ምርጫ ትዝብት ዋና አላማ በተደራጀ መልኩ የተሰበሰቡ መረጃዎችን በማቅረብ በምርጫው ሂደት ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ነበር። ይህንንም ለማሳካት CECOE በምርጫው ቀን ከቀኑ 5፡30 ላይ በተመደቡበት ምርጫ ጣቢያ የደረሱ ተቅማጭ ታዛቢዎችን አሰማርቷል።
የምርጫ ቁሳቁሶች መሟላት
የቅሬታ ማቅረቢያ ቅጽ ክጎደለብት ከሶማሌ ክልል በስተቀር ምርጫ በተካሄደባቸው እና ኅብረት ለምርጫ ታዛቢዎቸን ባሰማራባቸው ክልሎች የሚገኙ የምርጫ ጣቢያወች የትዝብት ግኝቶች የምርጫ ቁሳቁሶች ተሟልተው መገኝታቸውን ያሳያል። በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ተሞክሮዎች ጋር ሲነጻጸር በማነፃፀር የምርጫ ቁሳቁሶችን አሟልቶ በወቅቱ በማቅረብ የሚያስመሰግን ስራ አከናውኗል።
የምርጫ ጣቢያወች ተደራሽነት
የምርጫ ጣቢያዎች ተደራሽነት የተገለሉ የህብረተሰብ ክፍሎች በምርጫ ሂደት ውስጥ እንዲሳተፉ ያበረታታል፣ ክምርጫ ተሳትፎ የሚገለሉ ምራጮችን ይቀንሳል፣ በዚህም የመራጮች ተሳትፎ እንዲጨምር አስተዋጽኦ ያደርጋል። ኅብረት ለምርጫ ታዛቢዎችን ባሰማራባቸው ክልሎች የትዝብት ግኝቶች እንደሚያሳዩት የምርጫ ጣቢያዎች ለአካል ጉዳተኞች፣ ለነፍሰ ጡር እናቶች፣ ህጻናት ላሏቸው ሴቶች እና አረጋውያን ተደራሽ ነበሩ። ይህ መጠቀስ የሚገባው ሌላው አዎንታዊ መሻሻል ነው።
የምርጫ አስፈፃሚዎች የሥርዓተ-ፆታ ስብጥር እና ብዛት
የምርጫ አስፈጻሚወች ቁጥር እና የምርጫ አስፈጻሚወቹ የስርዓተ-ፆታ ስብጥር ኅብረቱ ታዛቢወቹን ያሰማራባቸው ክልሎች የሚጋሯቸው ጉዳዮች ነበሩ። በየድምጽ መስጫ ጣቢያ የምርጫ እስፈጻሚውች ቁጥር ከሞላ ጎደል አምስት እንዲሆን መደርጉ ክምርጫ ህጉ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ኅብረቱ መታዘብ ችሏል። ከአምስቱ የምርጫ አሰፈጻሚወች መካከል ቢያንስ ሁለቱ ሴቶች መሆናቸውንም የትዝብት ግኝቱ ያመለከታል። ክዚሀ በተጨማሪ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ሴት የምርጫ አስፈጻሚወች በዋና የምርጫ አስፈጻሚነት ማገልገላቸውንም ኅብረቱ መታዘብ ችሏል። ምንም እንኳ ቢያንስ ሶስት የምርጫ አስፈፃሚዎችን በየምርጫ ጣቢያው ማሰማራት ህጋዊ ቢሆንም፣ አምስት የምርጫ አስፈፃሚዎችን በየምርጫ ጣቢያው መሰማራታቸው የምርጫ ህጉ መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ የሚያሟላ በመሆኑ የሚያስመሰግን ተግባር ነው። መስፈርቱን ወጥነት ባለው መንገድ ማሟላት የምርጫ ህጉን ማክበር ነው። በሌላ በኩል የሴት ዋና ምርጫ ኦስፈጻሚወችን ብዛት ከፍ ለማድረግ ጥረት መደረግ ይኖርበታል፡፡
መጠለያ
ከምርጫ ጣቢያዎች ውጭ መጠለያ መኖር ድምጽ ለመስጠት ወረፋ ይዘው ተራችወን የሚጠብቁ መራጮችን ከዝናብ እና ከፀሀይ ለመከላከል ወሳኝ ነገር ነው። የምርጫ ጣቢያዎችን በሚዘጋጅበት ጊዜ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው አንዱ እና አስፈላጊው ነገር ቢኖር ወረፋ የሚጠብቁ መራጮች ከፀሐይ እና ከዝናብ የሚጠለሉብት መጠለያ ቦታ አለ ወይ? የሚለው ነው። ዝናባማ በሆነ ወቅት ለሚካሄዱ ምርጫዎች መጠለያ መኖር ይበልጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ዝናብ በሚዘንብበት ጊዜ መራጮች ዝናቡን ሽሽት ስልፋችውን በትነው በየፊናቸው የመሄድ ዕድላቸው ከፍተኛ ሲሆን በዚህ የተነሳ የመምረጥ መብታቸውን ሳይገለግሉብት ይቀራሉ። በአራቱም ክልሎች የተሰማሩት የ የኅብረቱ ታዛቢዎች አብዛኞቹ የምርጫ ጣቢያዎች ለመራጮች በቂ መጠለያ እንዳልነበራቸው ገልጸዋል።
የቅሪታ ስሚ ኮሚቴወች
የምርጫ ህጉ ለምርጫ ቦርድ ሶስት አባላት ያሉት ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎችን በምርጫ ጣቢያዎች እንዲያቋቁም ስልጣን ሰጥቶታል። ይሁን እንጂ በህጉ መሰረት ከተቋቋሙት ከጅግጅጋ ሁለት ምርጫ ጣቢያዎች (ጅ 06 ምርጫ ጣቢያ 02 እና ጂ 04 ምርጫ ጣቢያ 03) በስተቀር በአብዛኛዎቹ የምርጫ ጣቢያዎች የኅብረቱ ይታዘባችወ ቅሬታን ለመስማት የተቋቋሙት አብዛኛውቹ ኮሚቴዎች አንድም ከምርጫ ህጉ ጋር የማይጣጣሙ ናቸው አለያም ጨርሶ አልተቋቋሙም፡፡
የምርጫ ቅስቀሳ እና ያልተፈቀደላችው ስወች በምርጫ ጣቢያ ውስጥ መገኘት
የምርጫ ሀጉ ከምርጫ ጣቢያዎች 200 ሜትር ርቀት ውስጥ ቅስቀሳ ማድረግን በጥብቅ ይከለክላል፡፡ በጅግጅጋ በአንድ የምርጫ ጣቢያ (ጂ 09 ምርጫ ጣቢያ-3/ሀ)) ለብልጽግና ፓርቲ የሚቀሰቅሱ ግለሰቦች ከምርጫ ጣቢያው 20 ሜትር ርቀት ላይ ተስተውለዋል። በተመሳሳይ በአፋር ክልል በምርጫ ወቅት ያልተፈቀደላችው ግለሰቦች በተለይም የቀበሌ ባለስልጣናት በ"ገዋንኔ 01 ምርጫ ጣቢያ 01 ጋልኤብ ለ" ምርጫ ጣቢያ ውስጥ ተገኝተዋል።
የምርጫ ቅስቀሳ እና ያልተፈቀደላችው ስወች በምርጫ ጣቢያ ውስጥ መገኘት
የምርጫ ሀጉ ከምርጫ ጣቢያዎች 200 ሜትር ርቀት ውስጥ ቅስቀሳ ማድረግን በጥብቅ ይከለክላል፡፡ በጅግጅጋ በአንድ የምርጫ ጣቢያ (ጂ 09 ምርጫ ጣቢያ-3/ሀ)) ለብልጽግና ፓርቲ የሚቀሰቅሱ ግለሰቦች ከምርጫ ጣቢያው 20 ሜትር ርቀት ላይ ተስተውለዋል። በተመሳሳይ በአፋር ክልል በምርጫ ወቅት ያልተፈቀደላችው ግለሰቦች በተለይም የቀበሌ ባለስልጣናት በ"ገዋንኔ 01 ምርጫ ጣቢያ 01 ጋልኤብ ለ" ምርጫ ጣቢያ ውስጥ ተገኝተዋል።
የማንነት ማረጋገጫ ሳይኖር ድምጽ መስጠት
በአሶሳ ዞን በሚገኙ ሁለት ምርጫ ጣቢያዎች (አሶሳ 03 ምርጫ ጣቢያ 03 03 ሀ 2 እና ቡልደግሉ 01 ምርጫ ጣቢያ ቡልደግሉ ከተማ 01) ስማቸው በመራጭ መዝገብ ላይ ባይገኝም በአካል ጉዳተኝነት እና በእድሜ ምክንያት እንዲመርጡ የተፈቀደላቸው መሆኑን የኅብረቱ የትዝብት ግኝት ያሳያል። ክዚህ በተጨማሪ በምርጫ ህጉ ከተደነገገው አሰራር በተቃራኒ፣ በአፋር ክልል በሚገኝ አንድ የምርጫ ጣቢያ (ገዋንኔ 01 ምርጫ ጣቢያ ጋልኤብሃ) መራጮች የማንነት ማረጋገጫም ሆነ የምስክሮችን ቃል ሳያሰሙ እንዲመርጡ ተፈቅዶላቸዋል።
የመራጮች ጣት ላይ የማይለቅ ቀለም አለማድረግ
የምርጫ ህጉ መራጮቸ ድምጽ ከመስጠታችው በፊት የመራጮች ጣት በማይለቅ ቀለም እንዲቀልም የሚያስገድድ ቢሆንም በአሶሳ ዞን በሚገኝ አንድ ምርጫ ጣቢያ (አሶሳ 02 ምርጫ ጣቢያ 02 02 ሀ 1ለ) ሰባት መራጮች በጣቶቻቸው ላይ የማይለቅ የጣት ቀለም ሳይደረግላቸው እንዲመርጡ ተፈቅዶላቸዋል። በተመሳሳይ በአፋር ክልል በሶስት ምርጫ ጣቢያዎች ማለትም በአዋሬ እና ለምለምነን ምርጫ ጣቢያ 1 ግለሰብ፤ ደንበዲስ፣ ሃዶና ቢዳሪ ምርጫ ጣቢያ 8 ግለሰቦች እንዲሁም ሃዶ እና ከልዋን 01 ምርጫ ጣቢያ ከልዋን ከተማ 6 ግለሰቦች ጣቶቻቸውን በማይለቅ ቀለም ሳይቅልም አእንዲመርጡ ተደርጓል።
የድምጽ ቆጠራ መቋረጥ
አሶሳ 03 ምርጫ ጣቢያ 03 03 ሀ 2፣ አሶሳ 01 ምርጫ ጣቢያ 01 ሀ 2A፣ አሶሳ 02 ምርጫ ጣቢያ 02 02 ሀ 1B፣ እና አሶሳ 01 ምርጫ ጣቢያ 01 ለ 2 ፈንቲግራራ ምርጫ ጣቢያ ጉለሊ በምርጫ ቦርድ የተሰጠው የድምጽ አስጣጡ እስከ ምሽቱ 2 ሰአት መራዝሙን የተሰጠው መግለጫ ዘግየተው በመስማታቸው ፣የድምፅ ቆጠራው በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች እንዲቆም አድርጓል። የጣቢያዎቹን ስም ለመግለፅ ያክል ፣አሶሳ 03 ምርጫ ጣቢያ 03 03 ሀ 2፣ አሶሳ 01 ምርጫ ጣቢያ 01 ሀ 2A፣ አሶሳ 02 ምርጫ ጣቢያ 02 02 ሀ 1B፣ and አሶሳ 01 ምርጫ ጣቢያ 01 ለ 2ፈንቲግራራ ምርጫ ጣቢያ ጉለሊ።
File | Action |
---|---|
Amharic Preliminary Statement - Final Version (June 23).pdf | Download |