የትዝብት ሪፖርት በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ ም የተካሄዱ ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫዎች

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ (ኅብረት ለምርጫ) የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች በምርጫ ምልከታ እና ክትትል፣ በመራጮች ትምህርት አሰጣጥ ዙሪያ እና ከምርጫ በኋላ ሊከሰቱ የሚችሉ ግጭቶችን በመከላከል ላይ ያላቸውን ሚና ለማስተባበር እና ለማሳደግ የተመሰረተ ድርጅት ነው። ኅብረት ለምርጫ በሰኔ 16 2016 ዓ.ም የተካሄዱትን ቀሪን እና ድጋሚ ምርጫዎች ታዝቧል።

እነዚህ ምርጫዎች በአራት ክልሎች ማለትም ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ሶማሌ ክልሎች በሚገኙ የምርጫ ክልሎች ተካሂደዋል። የኅብረት ለምርጫ የምርጫ ታዛቢዎች የዚህን የምርጫ ሂደት ግልጽነት፣ ተጠያቂነት እና ከዴሞክራሲያዊ መርሆዎች ጋር አብሮ መሄድ የመታዘብ ዓላም ይዞ ነበር። ይህ ዋና ማጠቃለያ የምርጫ ሂደቶችን ከመታዘብ የተገኙ ግኝቶች እና ምክረ ሃሳቦችን የያዘ ነው። ኅብረት ለምርጫ 13 የረዥም ጊዜ ታዛቢዎችን ከግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ተሰማርተው የቅድመ ምርጫ ሂደቶችን ታዝበዋል። በድምጽ መስጫ ቀን ኅብረት ለምርጫ ተጨማሪ 77 ታዛቢዎችን ስልታዊ የሆነ የስምሪት መንገድን በመጠቀም አመቺ እና ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ አሰማርቷል።

ታዛቢዎች ቀድመው የተዘጋጁ ቅጾችን በመጠቀም በቅድመ ምርጫ፣ በድምጽ መስጫ ቀን እና በድህረ ምርጫ ሂደቶች ላይ ያገኟቸውን ከመራጮች ትምህርት፣ የቅስቀሳ ተግባራት፣ የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች አደረጃጀት፣ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቶች ፣ የድምጽ ቆጠራ ጋር የተገናኙ የትዝብት ግኝቶችን አሰባስቧል።

FileAction
June 24 election CECOE- Observation Report_Amh_V1.pdfDownload