ይህ የፖሊሲ ማብራሪያ በመገናኛ ብዙሃን እና በምርጫ መካከል ያለውን ግንኙነት አስፈላጊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በኢትዮጵያ 6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዙሪያ ያሉትን ተግዳሮቶች፣ አንድምታዎች እና ተስፋዎች እና የመገናኛ ብዙሃን የተለያዩ የምርጫ ባለድርሻ አካላትን ተደራሽነት ይዳስሳል። ከዚህ ባለፈም የሚዲያ ተቋማት የጋዜጠኝነት ሞያ ስነ-ምግባር አክብረው በምርጫው ሂደት ላይ ሚዛናዊ ሽፋን መስጠት እንዳለባቸው ያትታል። በተጨማሪም የመራጮች ትምህርት የሚዲያ ሽፋን ማሳደግ እና ሴቶችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በምርጫ ወቅት በሚዲያ ሽፋን በበቂ ሁኔታ እንዲወከሉ የማድረግን አስፈላጊነት አጉልቶ ያሳያል።

በኅብረት ለምርጫ የሚዲያ ክትትል ክፍል ዘገባ ላይ በመመስረት፤ 6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ በተካሄደበት ወቅት፣ ከምርጫ ጋር የተያያዙ ርዕሰ ጉዳዮች ብዙውን ጊዜ በመገናኛ ብዙኃን ሽፋን ቢያገኙም፤ ነገር ግን የሚዲያ ሽፋን በሌሎች ከምርጫ ጋር ያልተገናኙ የፖለቲካ ጉዳዮች () አብላጫ የሆኖ ሽፋን አግኝተው ነበረ። በምርጫ ክርክሮች ላይ 12 የፖለቲካ ፓርቲዎች ቢሳተፉም በትላልቅ የክርክር መድረኮች 5 የፖለቲካ ፓርቲዎች ብቻ ነበር የተሳተፉት። የጋዜጠኝነት ሞያዊ ሥነ ምግባርን አክብሮ መዘገብ ላይ ከሚዲያ ሚዲያ ልዩነት ነበረ። ከዚህም ባለፈ አብዛኛው ሚዲያ የምርጫ ቅስቀሳን ሚዛናዊነት በጠበቀ መልኩ ከመገናኛ ብዙሀን ህጎች እና ከምርጫ ቦርድ መመሪያዎች ጋር በተስማማ ሁኔታ ማቅረብ አልቻሉም ነበር። ገዥው ብልፅግና ፓርቲ ከሌሎች የምርጫ ባለድርሻ አካላት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛውን ሽፋን ያገኘ ሲሆን በተጨማሪም ሚዲያዎች ከምርጫ ጋር በተገናኘ ለሴቶች የሰጡት ሽፋን በጣም አነስተኛ ነበር፡፡

በኢትዮጵያ የሚዲያ ዘርፍ በምርጫ ወቅት ተገቢውን ሚና እንዲጫወት ለማድረግ ከቀደምት የስኬት ተሞክሮዎች ትምህርት በመውሰድ እና በመጪው ምርጫ የሚዲያው ዘርፍ የላቀ ሚና እንዲኖረው መሻሻል በሚገባቸው ዘርፎች ላይ አተኩሮ ሊሰራ ይገባል። ይህ ካልሆነ ግን ሚናው ተቆርጦ በቀደመው ምርጫ ወቅት እንደነበረው ይቆያል።

FileAction
CECOE Policy Brief Ethiopian Media Accessibility amharic .pdfDownload