በ2013 ዓ.ም የተካሄደው የኢትዮጵያ ስድስተኛው አገር አቀፍ እና የክልል ምክር ቤቶች ምርጫ በአገሪቱ ከ2010 ዓ.ም አንስቶ የሚታዩትን ዲሞክራሲያዊ ጅማሮዎች ለማስቀጠል ወሳኝ መሰረትን ጥሏል። በአዲስ መልክ የተቀረፀው የምርጫ ህግና የቁጥጥር ማዕቀፍ ምርጫው ይበልጥ ንቁ የፖለቲካ ፉክክር እንዲታይበት፣ የዳኝነት አካሉ በምርጫ ሂደቱ ወሳኝ ሚናን እንዲጫወት እና ፣ ለሲቪል ማህበረሰቡ ተሳትፎ ሰፋ ያለ ምህዳር እንዲኖር አስችሏል። በተጨማሪም በ2013 ዓ.ም የተከናወነው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ የሲቪል ማኅበራት በምርጫ ታዛቢነት እንዲሳተፉ በማስቻል በምርጫ ሂደቱ ላይ ትርጉም ያላቸው ግምገማዎችን እንዲያደርጉ ያስቻለ ምርጫ ሆኖ አልፏል። ከእነዚህ ለውጦች ጋር በተያያዘ ምርጫው የኢትዮጵያ ዜጎችን ጨምሮ በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በሲቪል ማኅበራት እና በተለያዩ ባለድርሻ አካላት ዘንድ ካለፉት ምርጫዎች ይልቅ የበለጠ አካታች፣ ተጠያቂነትና ግልጽነት የሰፈነበት ይሆናል ተብሎ እንዲጠበቅ አድርጐታል። ምንም እንኳን በቅድመ ምርጫ፣ የድምፅ መስጫ ቀንና በድኅረ ምርጫ ሂደቶች ወቅት በግልጽ ጉድለቶች ቢስተዋሉም፤ በምርጫው ሂደት ህብረቱ የታዘባቸው ትርጉም ያላቸው መሻሻሎች አገሪቱ በቀጣይ ለምታደርጋቸው ምርጫዎች መሠረት ጥሎ አልፏል።
File | Action |
---|---|
amharic cecoe final report.pdf | Download |