የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ (ኅብረት ለምርጫ) በመጋቢት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ትኩረቱን በ6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ወቅት በሲቪል ማህበራት አማካኝነት የተሰጠውን የመራጮች ትምህርት አስመልክቶ ባስጠናው ጥናት ላይ የምክክር መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። በመድረኩ ላይም ወደ ሀምሳ (50) የሚጠጉ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍል የተውጣጡ ተሳታፊዎች ታድመው ነበር። የመድረኩ ዋና አላማም ኅብረት ለምርጫ በመራጮች ትምህርት ዙሪያ ላይ ያካሄደውን ጥናት ግኝቶችን ከሲቪል ማህበራት ለተውጣጡ ተሳታፊዎች ለማጋራትን እና አስተያየታቸውን ለመቀበል ነበር። ከስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በፊት የተደረጉ ማሻሻያዎች በ1997 ዓ.ም የተካሄደውን አወዛጋቢውን ሶስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት ተግባራዊ ያደረገው “አፋኙ” የምርጫ ሕግ እንዲሁም የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህግ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች በምርጫ ሂደት ውስጥ የነበራቸው ተሳትፎ በእጅጉ ወስኖታል። በዚህ ህግ ውስጥ ተቀምጠው የነበሩ የገንዘብ ምንጭ እና የዘርፍ ክልከላዎችዎች የሲቪል ማህበራት ከምርጫ ጋር የተገናኙ ተግባራትን እንዳያከናውኑ እክል ፈጥሮባቸው ነበር። በተመሳሳይ መልኩም ቀድሞ በተግባር ላይ ሲውል የነበረው የምርጫ የህግ ማዕቀፍ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶችን በመራጮች ትምህርት እና ከምርጫ ትዝብት ሥራዎች ላይ በተመሳሳይ ወቅት እንዳይሳተፉ በመከልከ ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች ከሁለቱ ወሳኝ የምርጫ ክንውኖች ውስጥ አንዱን ብቻ መርጠው እንዲሳተፉ ያስገድድ ነበር። በዚህ ገደብ የተነሳም የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች በቀጣይነት በተካሄዱት በአራተኛው እና አምስተኛውን ጠቅላላ ምርጫዎች ላይ የነበራቸው ሚና በጣም ውስን ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ቀድመው በተከናወኑ የህግ ማሻሻያዎች አማካኝነት የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች በምርጫ ላይ የነበራቸው ተሳትፎ በጥሩ መልኩ ሊሻሻል ችሏል። በሚያስደንቅ መልኩም ሀገር በቀል የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች እራሳቸውን በማደራጀት በምርጫው ሂደት ላይ ለመሳተፍ ችለዋል። በዚህም መሰረት 167 የሚጠጉ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች የመራጮች ትምህርት እንዲሰጡ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ተሰጥቷቸው ነበር። ሆኖም ግን የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች የመራጮች ትምህርት በሚሰጡበት ወቅት ቅቡልነት ከማጣት (legitimacy)፣ ውጤታማ የሆነ የመራጮች ትምህርት ፕሮጀከት ለመቅረፅ የችሎታ

FileAction
CECOE Policy Brief Ethiopian Media Accessibility amharic .pdfDownload