በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ክልሎች የተካሄደውን ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት የመጀመሪያ ደረጃ የትዝብት ሪፖርት

በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ክልሎች የተካሄደውን ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት የመጀመሪያ ደረጃ የትዝብት ሪፖርት

የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ (ኅብረት ለምርጫ) ከ175 በላይ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበራትን ያቀፈ ኅብረት ነው። ኅብረቱ ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ እና ገለልተኛ የሆነ የዜጎች የምርጫ ታዛቢ ቡድን ሲሆን ዋና ዓላማውም  በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉን አቀፍ፣ ግልጽ እና በተጠያቂነት ምርጫዎች እንዲከናወኑ አስተዋጽኦ ማድረግ ነው። 

በ2010 ዓም የተጀመረው የፖለቲካ ማሻሻያ ሂደት የተለያዩ የህግ እና ተቋማዊ ማሻሻያዎችን አድርጓል። ከተካሄዱት ማሻሻያዎች መካከል ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት የምርጫ ሕጉን ማሻሻል፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን እንደገና ማቋቋም፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ ሥርዓትን መከለስ እና አጠቃላይ የምርጫ ሁኔታን ማሻሻል ይገኙበታል። ምንም  እንኳ እነዚህ ማሻሻያዎች ቢደረጉም በትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች የዴሞክራሲ ተሃድሶው ሂደቱን የሚያውኩ ብቻ ሳይሆን ክላይ በተዘረዘሩት ከለሎች  በ2013 ዓም በተካሄደውአጠቃላይ ምርጫ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድሩ  አፋሳሸ ግጭቶች ተከስተዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ምርጫ ቦርድ በቀድሞው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል እና የሶማሌ ክልል አንዳንድ የምርጫ ክልሎች በምርጫ ሂደቱ ላይ በታዩ ከፍተኛ  ጉድለቶች ምክንያት የምርጫ ውጤቱን ሰርዟል። በዚህም ምክንያት የተወሰኑ  የፌደራል ፓርላማ እና የክልል ምከር ቤቶች መቀመጫዎች ክፍት ሆነው ቆይተዋል።

ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ባልተከናወነባቸው አካባቢዎች እና ድጋሚ ምርጫ እንዲከናወንባቸው በቦርዱ ውሳኔ በተሰጠባቸው የምርጫ ክልሎች በተለይም በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ እፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ምርጫን ማድራጅት  አስፈላጊ በመሆኑ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫዎችን በአራቱ ክልሎች እንደሚያከናውን ማሳወቁ እና  ፤በመጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ቦርዱ የቀሪ እና ድጋሚ ምርጫዎች የሚካሄዱበትን የምርጫ የጊዜ ሠሌዳ ለህዝብ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።  በዚህ የጊዜ ሠሌዳ መሰረት ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም የድምጽ መስጫ ቀን እንዲሆን ተወስኖ የነበረ ቢሆንም ቦርዱ የምርጫው  ቀን ወደ ሰኔ 09 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲተላለፍ አድርጓል። ነገር ግን  ሰኔ 09 ቀን 2016 ዓ.ም ከዋለው የኢድ አል አድሃ ኃይማኖታዊ ክብረ በዓል ጋር በመገጣጠሙ  ቦርዱ የድምጽ መስጫ ቀኑን በድጋሚ ወደ ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም አዘዋውሮታል። ከምርጫ ቦርድ በተገኘው  መረጃ ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚካሄዱት ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫዎች በአጠቃላይ 1258 የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች (ከነዚህ ውስጥ 578 በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ 388 በአፋር፣ 123 በሶማሌ እንዲሁም 169 የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች እንደሚያቋቁም ገልጿል።

የትዝብት ግኝቶች አጭር ማጠቃልያ

ሰኔ 16 ቀን 2024 የተካሄደውን ቀሪ ምርጫ እና ድጋሚ ምርጫ ትዝብት   ዋና አላማ በተደራጀ መልኩ የተሰበሰቡ መረጃዎችን በማቅረብ በምርጫው ሂደት ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ነበር። ይህንንም ለማሳካት CECOE በምርጫው ቀን ከቀኑ 5፡30 ላይ በተመደቡበት ምርጫ ጣቢያ የደረሱ ተቅማጭ ታዛቢዎችን አሰማርቷል።

  የምርጫ ቁሳቁሶች መሟላት

የቅሬታ ማቅረቢያ ቅጽ ክጎደለብት ከሶማሌ ክልል በስተቀር  ምርጫ በተካሄደባቸው እና ኅብረት ለምርጫ ታዛቢዎቸን ባሰማራባቸው ክልሎች የሚገኙ የምርጫ ጣቢያወች የትዝብት ግኝቶች የምርጫ ቁሳቁሶች ተሟልተው መገኝታቸውን  ያሳያል። በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ተሞክሮዎች ጋር ሲነጻጸር በማነፃፀር የምርጫ ቁሳቁሶችን አሟልቶ በወቅቱ በማቅረብ የሚያስመሰግን ስራ አከናውኗል።

 የምርጫ ጣቢያወች ተደራሽነት

የምርጫ ጣቢያዎች ተደራሽነት የተገለሉ የህብረተሰብ ክፍሎች በምርጫ ሂደት ውስጥ እንዲሳተፉ ያበረታታል፣ ክምርጫ ተሳትፎ የሚገለሉ ምራጮችን ይቀንሳል፣ በዚህም የመራጮች ተሳትፎ እንዲጨምር አስተዋጽኦ ያደርጋል። ኅብረት ለምርጫ  ታዛቢዎችን ባሰማራባቸው ክልሎች የትዝብት ግኝቶች እንደሚያሳዩት የምርጫ ጣቢያዎች ለአካል ጉዳተኞች፣ ለነፍሰ ጡር እናቶች፣ ህጻናት ላሏቸው ሴቶች እና አረጋውያን ተደራሽ ነበሩ። ይህ መጠቀስ  የሚገባው ሌላው አዎንታዊ መሻሻል ነው።

የምርጫ አስፈፃሚዎች የሥርዓተ-ፆታ ስብጥር እና ብዛት

የምርጫ አስፈጻሚወች  ቁጥር  እና የምርጫ አስፈጻሚወቹ  የስርዓተ-ፆታ  ስብጥር ኅብረቱ ታዛቢወቹን ያሰማራባቸው ክልሎች  የሚጋሯቸው   ጉዳዮች ነበሩ።  በየድምጽ መስጫ ጣቢያ የምርጫ እስፈጻሚውች  ቁጥር  ከሞላ ጎደል አምስት እንዲሆን መደርጉ ክምርጫ ህጉ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ኅብረቱ መታዘብ ችሏል።  ከአምስቱ የምርጫ አሰፈጻሚወች  መካከል ቢያንስ ሁለቱ ሴቶች መሆናቸውንም የትዝብት ግኝቱ ያመለከታል። ክዚሀ በተጨማሪ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ሴት የምርጫ አስፈጻሚወች  በዋና የምርጫ አስፈጻሚነት  ማገልገላቸውንም ኅብረቱ መታዘብ ችሏል። ምንም እንኳ ቢያንስ ሶስት የምርጫ አስፈፃሚዎችን በየምርጫ ጣቢያው ማሰማራት ህጋዊ ቢሆንም፣  አምስት የምርጫ አስፈፃሚዎችን በየምርጫ ጣቢያው  መሰማራታቸው የምርጫ ህጉ መስፈርቶችን  ሙሉ በሙሉ የሚያሟላ በመሆኑ  የሚያስመሰግን  ተግባር ነው። መስፈርቱን ወጥነት ባለው መንገድ ማሟላት የምርጫ ህጉን ማክበር ነው። በሌላ በኩል የሴት ዋና ምርጫ ኦስፈጻሚወችን  ብዛት  ከፍ ለማድረግ ጥረት መደረግ ይኖርበታል፡፡

 መጠለያ

ከምርጫ ጣቢያዎች ውጭ መጠለያ መኖር  ድምጽ ለመስጠት ወረፋ ይዘው ተራችወን   የሚጠብቁ መራጮችን ከዝናብ እና ከፀሀይ ለመከላከል  ወሳኝ ነገር ነው። የምርጫ ጣቢያዎችን በሚዘጋጅበት ጊዜ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው አንዱ እና አስፈላጊው ነገር ቢኖር ወረፋ የሚጠብቁ መራጮች ከፀሐይ እና ከዝናብ የሚጠለሉብት መጠለያ ቦታ አለ ወይ? የሚለው ነው። ዝናባማ በሆነ ወቅት ለሚካሄዱ ምርጫዎች መጠለያ መኖር ይበልጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ዝናብ በሚዘንብበት ጊዜ መራጮች  ዝናቡን ሽሽት  ስልፋችውን በትነው በየፊናቸው የመሄድ ዕድላቸው ከፍተኛ ሲሆን በዚህ የተነሳ  የመምረጥ መብታቸውን ሳይገለግሉብት ይቀራሉ።  በአራቱም ክልሎች የተሰማሩት የ የኅብረቱ ታዛቢዎች አብዛኞቹ የምርጫ ጣቢያዎች ለመራጮች በቂ መጠለያ እንዳልነበራቸው ገልጸዋል።

 የቅሪታ ስሚ ኮሚቴወች

የምርጫ ህጉ ለምርጫ ቦርድ ሶስት አባላት ያሉት ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎችን በምርጫ ጣቢያዎች እንዲያቋቁም ስልጣን ሰጥቶታል። ይሁን እንጂ በህጉ መሰረት ከተቋቋሙት ከጅግጅጋ ሁለት ምርጫ ጣቢያዎች (ጅ 06 ምርጫ ጣቢያ 02 እና ጂ 04 ምርጫ ጣቢያ 03) በስተቀር በአብዛኛዎቹ የምርጫ ጣቢያዎች የኅብረቱ ይታዘባችወ ቅሬታን ለመስማት የተቋቋሙት አብዛኛውቹ ኮሚቴዎች አንድም ከምርጫ ህጉ ጋር የማይጣጣሙ ናቸው አለያም ጨርሶ አልተቋቋሙም፡፡

 የምርጫ ቅስቀሳ እና ያልተፈቀደላችው ስወች በምርጫ ጣቢያ ውስጥ መገኘት

የምርጫ ሀጉ ከምርጫ ጣቢያዎች 200 ሜትር ርቀት  ውስጥ ቅስቀሳ ማድረግን በጥብቅ ይከለክላል፡፡ በጅግጅጋ በአንድ የምርጫ ጣቢያ (ጂ 09 ምርጫ ጣቢያ-3/ሀ))  ለብልጽግና ፓርቲ የሚቀሰቅሱ  ግለሰቦች ከምርጫ ጣቢያው  20 ሜትር ርቀት ላይ ተስተውለዋል። በተመሳሳይ በአፋር ክልል በምርጫ ወቅት ያልተፈቀደላችው ግለሰቦች በተለይም የቀበሌ ባለስልጣናት በ”ገዋንኔ 01 ምርጫ ጣቢያ 01 ጋልኤብ ለ” ምርጫ ጣቢያ ውስጥ ተገኝተዋል።

 የምርጫ ቅስቀሳ እና ያልተፈቀደላችው ስወች በምርጫ ጣቢያ ውስጥ መገኘት

የምርጫ ሀጉ ከምርጫ ጣቢያዎች 200 ሜትር ርቀት  ውስጥ ቅስቀሳ ማድረግን በጥብቅ ይከለክላል፡፡ በጅግጅጋ በአንድ የምርጫ ጣቢያ (ጂ 09 ምርጫ ጣቢያ-3/ሀ))  ለብልጽግና ፓርቲ የሚቀሰቅሱ  ግለሰቦች ከምርጫ ጣቢያው  20 ሜትር ርቀት ላይ ተስተውለዋል። በተመሳሳይ በአፋር ክልል በምርጫ ወቅት ያልተፈቀደላችው ግለሰቦች በተለይም የቀበሌ ባለስልጣናት በ”ገዋንኔ 01 ምርጫ ጣቢያ 01 ጋልኤብ ለ” ምርጫ ጣቢያ ውስጥ ተገኝተዋል።

 

 የማንነት ማረጋገጫ ሳይኖር ድምጽ መስጠት

በአሶሳ ዞን በሚገኙ ሁለት ምርጫ ጣቢያዎች (አሶሳ 03 ምርጫ ጣቢያ 03 03 ሀ 2 እና ቡልደግሉ 01 ምርጫ ጣቢያ ቡልደግሉ ከተማ 01) ስማቸው በመራጭ መዝገብ ላይ ባይገኝም በአካል ጉዳተኝነት እና በእድሜ ምክንያት እንዲመርጡ የተፈቀደላቸው መሆኑን የኅብረቱ የትዝብት ግኝት ያሳያል። ክዚህ በተጨማሪ በምርጫ ህጉ ከተደነገገው አሰራር በተቃራኒ፣ በአፋር ክልል በሚገኝ አንድ የምርጫ ጣቢያ (ገዋንኔ 01 ምርጫ ጣቢያ ጋልኤብሃ) መራጮች የማንነት ማረጋገጫም ሆነ የምስክሮችን ቃል ሳያሰሙ እንዲመርጡ ተፈቅዶላቸዋል።

 የመራጮች ጣት ላይ የማይለቅ  ቀለም  አለማድረግ

 የምርጫ ህጉ መራጮቸ ድምጽ ከመስጠታችው  በፊት የመራጮች ጣት በማይለቅ ቀለም እንዲቀልም  የሚያስገድድ ቢሆንም በአሶሳ ዞን በሚገኝ አንድ ምርጫ ጣቢያ (አሶሳ 02 ምርጫ ጣቢያ 02 02 ሀ 1ለ) ሰባት መራጮች በጣቶቻቸው ላይ የማይለቅ የጣት ቀለም ሳይደረግላቸው እንዲመርጡ ተፈቅዶላቸዋል። በተመሳሳይ በአፋር ክልል በሶስት ምርጫ ጣቢያዎች ማለትም በአዋሬ እና ለምለምነን ምርጫ ጣቢያ  1 ግለሰብ፤ ደንበዲስ፣ ሃዶና ቢዳሪ ምርጫ ጣቢያ 8 ግለሰቦች እንዲሁም  ሃዶ እና ከልዋን 01 ምርጫ ጣቢያ ከልዋን ከተማ  6 ግለሰቦች ጣቶቻቸውን በማይለቅ ቀለም ሳይቅልም አእንዲመርጡ ተደርጓል።

 የድምጽ ቆጠራ መቋረጥ

አሶሳ 03 ምርጫ ጣቢያ 03 03 ሀ 2፣ አሶሳ 01 ምርጫ ጣቢያ 01 ሀ 2A፣ አሶሳ 02 ምርጫ ጣቢያ 02 02 ሀ 1B፣ እና አሶሳ 01 ምርጫ ጣቢያ 01 ለ 2 ፈንቲግራራ ምርጫ ጣቢያ ጉለሊ በምርጫ ቦርድ  የተሰጠው  የድምጽ አስጣጡ እስከ ምሽቱ 2 ሰአት መራዝሙን የተሰጠው መግለጫ  ዘግየተው በመስማታቸው ፣የድምፅ ቆጠራው በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች እንዲቆም አድርጓል። የጣቢያዎቹን ስም ለመግለፅ ያክል ፣አሶሳ 03 ምርጫ ጣቢያ 03 03 ሀ 2፣ አሶሳ 01 ምርጫ ጣቢያ 01 ሀ 2A፣ አሶሳ 02 ምርጫ ጣቢያ 02 02 ሀ 1B፣ and አሶሳ 01 ምርጫ ጣቢያ 01 ለ 2ፈንቲግራራ ምርጫ ጣቢያ ጉለሊ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ የዕጩዎች ጥቆማ፣ አመራረጥ እና ሹመት ሂደት የክትትል ሪፖርት

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ የዕጩዎች ጥቆማ፣ አመራረጥ እና ሹመት ሂደት የክትትል ሪፖርት

መግቢያ

የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ (ኅብረት ለምርጫ) በ2011 የተቋቋመ ሲሆን የሲቪል ማህበራት በምርጫ ትዝብት ፣ ክትትል፣  የመራጮች ትምህርት እና ከምርጫ በኋላ ግጭቶችን በመከላከል ላይ ያላቸውን ሚና ለማሳደግ እና ለማስተባበር የተቋቋመ ነው። ኅብረት ለምርጫ በተመሰረተ ማግስት የሲዳማ ህዝበ ውሳኔን በተቀናጀ መልኩ በመታዘብ በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ዘርፍ ውስጥ አዲስ ምዕራፍን ከፍቷል። ይህንን ልምድ በመቀመር በስድስተኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ እና ክልላዊ ምርጫ ኅብረት ለምርጫ ከ3,500 በላይ የረጅም ጊዜ እና የአጭር ጊዜ ታዛቢዎችን በዘጠኝ ክልሎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች መልምሎ በማሰልጠን አሰማርቷል። ይህም ሰኔ 2013 ዓ.ም እና መስከረም 2014 ዓ.ም በተካሄደው ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝበ ውሳኔ የተካሄዱትን ምርጫዎች ያካትታል። በመቀጠልም በጥር ወር 2015 ዓ.ም በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የተካሄደውን ህዝበ ውሳኔ እና በሰኔ 19 ቀን 2015 ዓ.ም የተካሄደውን የወላይታ ዞን ድጋሚ ህዝበ ውሳኔ በተሳካ ሁኔታ ታዝቧል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን እና አዲስ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሹመትን ወሳኝነት በመገንዘብ ኅብረቱ የምርጫ ቦርድን ሰብሳቢ የአመላመል እና ሹመት ሂደት በቅርበት ተከታትሏል።  ይህ የግምገማ ሪፖርት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢን ምልመላ፣ አመራረጥ እና የሹመት ሂደት እንዲሁም ሂደቱ ሕጉን የተከተለ ስለመሆኑ በሚዲያ የወጡ ሪፖርቶች እና መልማይ ኮሚቴው በሰጣቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች ላይ በመመስረት በዝርዝር ፈትሿል። ሪፖርቱ እንደ ግልፅነት፣ አካታችነት እና አሳታፊነት ያሉ ዋና ዋና የፖለቲካ ሂደትን መመዘኛዎችን በመጠቀም ለወደፊት ለሚከናወኑ የአሿሿም ሂደት ለማሻሻል ምክረ-ሃሳቦች ለመስጠት ሞክሯል። ይህም የዲሞክራሲያዊ መርሆዎችን ለማስከበር፣ ዜጎች በምርጫ ሥርዓቱ ላይ እምነት እንዲያድርባቸው፣ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አመራረጥን በተመለከተ ግልጽና በበቂ መረጃ ላይ የተመሰረተ ውይይት ለማድረግ የበኩሉን አስተዋጽዖ በማበርከት፣ በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ምርጫዎች ተዓማኒነት እና ቅቡልነት ለማረጋገጥ ቁልፍ አስተዋጽዖ ይኖረዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝበ-ውሳኔ እና የወላይታ ዞን ድጋሚ ሕዝበ-ውሳኔ  አጠቃላይ የትዝብት ሪፖርት

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝበ-ውሳኔ እና የወላይታ ዞን ድጋሚ ሕዝበ-ውሳኔ አጠቃላይ የትዝብት ሪፖርት

በኢፌዲሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 47 (2) በአንቀጽ 47 (1) በተዘረዘሩት ክልሎች ውስጥ የተካተቱት ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የራሳቸውን ክልል የመመሥረት መብት ክልል የመመሥረት ጥያቄው በብሔሩ፣ በብሔረሰቡ ወይም በሕዝቡ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ተቀባይነት ማግኘቱ ሲረጋገጥ እና ጥያቄው በጽሑፍ ለክልሉ ምክር ቤት ሲቀርብ፣ ጥያቄው የቀረበለት የክልል ምክር ቤትም ጥያቄው በደረሰው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለጠየቀው ብሔር ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ ሕዝበ ውሳኔ ሲያደራጅ፣ ክልል የመመሥረት ጥያቄው ሕዝበ ውሳኔውን ባካሄደው ብሔር፣ ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ በአብላጫ ድምፅ ድጋፍ ሲያገኝ፣ እና የክልሉ ምክር ቤት የክልልነት ጥያቄ ላቀረበው ብሔር፣ ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ ሥልጣን ሲያስረክብ ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች ከተሟሉ በሕዝበ ውሳኔው የሚፈጠረው አዲስ ክልል ጥያቄ ማቅረብ ሳያስፈልገው በቀጥታ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አባል እንደሚሆን ሕገ መንግሥቱ ይደነግጋል።

ባለፉት አራት አመታት ውስጥ የደቡብ ክልል ሶስት የክልልነት ህዝበ ውሳኔዎች የተካሄዱ ሲሆን ይህ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ያካሄዱት ሕዝበ- ውሳኔ ሶስተኛው ነው። የደቡብ ክልል በ2012 ዓ.ም የሲዳማ ሕዝበ-ውሳኔን፣ በ2014 ዓ.ም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሕዝበ-ውሳኔን ማስተናገዱ የሚታወስ ነው። የስድስቱ ዞኖች እና አምስቱ ልዩ ወረዳዎች የክልልነት ጥያቄ ለፌዴሬሽን ምክርቤት የቀረበው የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝበ-ውሳኔ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል ላይ የሚነሱ የክልልነት ጥያቄዎችን መፍትሄ እንዲያፈላጉ የተሾሙ የሰላም አምባሳደሮች1 ባደረጉት አነሳሽነት እና የስድስቱ ዞኖች እና አምስቱ ልዩ ወረዳዎች ምክር ቤቶች ለፌደሬሽን ምክርቤት ባቀረቡት ማመልከቻ መሰረተ ነው። የፌደሬሽን ምክር ቤት የቀረበለትን ጥያቄ ተቀብሎ አጸድቆ ለኢትዬጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕዝበ-ውሳኔውን እንዲያስፈጽም ትዕዛዝ ማስተላለፉን ተከትሎ ሕዝበ- ውሳኔው ተግባራዊ ሆኗል።

ኅብረት ለምርጫም በደቡብ ክልል ለሶስተኛ ጊዜ የተካሄደውን የሕዝበ-ውሳኔ ወሳኝ ሂደቶችን ማለትም የቅድመ- ሕዝበ ውሳኔን፣ የሕዝበውሳኔ ምርጫ ቀንን እንዲሁም ድህረ-ሕዝበ ውሳኔን ታዝቧል። በተጨማሪም በወላይታ ዞን የተካሄደውን የደጋሚ ህዝበ ውሳኔ ሂደት ታዝቧል። በዚህም መሰረት ኅብረት ለምርጫ በትዝብት ሥራው የደረሰባቸውን አንኳር ግኝቶች በሚከተለው ክፍል ይዳስሳል።

በኢትዮጵያ የምርጫ ቅሬታ አሰማም ዘዴ ላይ የተዘጋጀ  የኅብረት ለምርጫ ፖሊሲ ፍሬ ሃሳብ

በኢትዮጵያ የምርጫ ቅሬታ አሰማም ዘዴ ላይ የተዘጋጀ የኅብረት ለምርጫ ፖሊሲ ፍሬ ሃሳብ

ከምርጫ ጋር በተገናኘ የሚነሱ ቅሬታዎችን በወቅቱ እና በአግባቡ ለመፍታት የምርጫ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎችን (Grievance Hearing Committees) በተፈላጊው መጠን መመስረት እና ተግባራዊ እንዲሆኑ ማድረግ ወሳኝ ነው። የእነዚህን ኮሚቴዎች ውጤታማነት እና ቅልጥፍና ማረጋገጥ የተግባራዊነት መስፈርቶችን ከአቤቱታ አቅራቢዎች መብት ጋር የሚያመዛዝን ተግባራዊ የህግ ማዕቀፍ ማውጣትን ይጠይቃል። የኢትዮጵያ ምርጫ አዋጅ እና ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች ማቋቋሚያ እና አሰራር መመሪያ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች በምርጫ ጣቢያ፣ በምርጫ ክልል እና በክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ደረጃ ባሉ የምርጫ አፈጻጸም መዋቅሮች ላይ ሶስት ሶስት አባላት ያሏቸው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎችን ያቋቋማሉ።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (ቦርዱ) በህግ የተቋቋሙትን ኮሚቴዎች በአግባቡ መጠቀም አለመቻሉን የኅብረት ለምርጫ የስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ትዝብት ሪፖርት ያሳያል። በዚህም የተነሳ ቅሬታ አቅራቢዎች (መራጮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሌሎች) ከሕግ ውጪ ለሆኑ አሰራሮች እንደተጋለጡ የኅብረት ለምርጫ ትዝብት ያመለክታል። በስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጾችን ከማጣራት እና ከመቁጠር ጋር የተያያዙ ቅሬታዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችን ፣የፓርቲ ተወካዮችን ከምርጫ ቆጠራ ሂደት ማባረር፣ መራጮችን ማስፈራራት፣ የገዥው ፓርቲ አባላት ጣልቃ ገብነት፣ በተንቀሳቃሽ የምርጫ ታዛቢነት እንዳይሳተፉ በባለሥልጣናት/ በአስተዳዳሪዎች መገደብ የመሳሰሉት ቅሬታዎች ቀርበው ነበር።

ይህ የፖሊሲ ፍሬ ሃሳብ በፖሊሲ አውጪዎች በተለይም ቦርዱ በኢትዮጵያ የምርጫ ቅሬታ አሰማም ዘዴ ላይ የፖሊሲ ማሻሻያ ለማድረግ አሳማኝ ሃሳብ ለማቅረብ ያለመ ነው። በዚህ ሰነድ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች እና ለሲቪል ማህበራት ድርጅቶች የተለያዩ ምክረ-ሃሳቦች ተሰጥተዋል። በዚህም መሰረት ቦርዱ አሁን በሕግ የተደነገገው የምርጫ ቅሬታ አሰማም ሂደት ካሉበት ተግባራዊ ውሱንነት አንፃር በማሻሻል የቅሬታ አሰማም ሂደቶች ተግባራዊ መሆናቸውን ሊያረጋግጥ ይገባል። ፖለቲካ ፓርቲዎች ቅሬታቸውን በሚያቀርቡበት ጊዜ ሁሉንም የሕግ እና የተቋም መስፈርቶች የሚከተሉ እንዲሆኑ አቅማቸውን ማሳደግ። በተጨማሪም የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች አባላትን በመመልመል እና በማሰልጠን ለምርጫ ቦርድ ድጋፍ ማድረግ አለባቸው። ከዚህም ባለፈ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች የኢትዮጵያ የምርጫ ቅሬታ አሰማም ዘዴ ሕግን የሚመለከቱ ስልጠናዎችን ለፖለቲካ ፓርቲዎች መስጠት አለባቸው።

የኅብረት ለምርጫ ምልከታ በ6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ቦርድ የምርጫ ሰራተኞች ምልመላ እና ስልጠና ጥራት

የኅብረት ለምርጫ ምልከታ በ6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ቦርድ የምርጫ ሰራተኞች ምልመላ እና ስልጠና ጥራት

በኢትዮጵያ ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እና መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን፤ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በክልል ምክር ቤቶች ለአምስት ዓመታት የሚያገለግሉ የህዝብ ተወካዮች ተመርጠዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ ውስጥ ምርጫ እንዲያዘጋጅ ህጋዊ ስልጣን የተሰጠው ሲሆን፤ በምርጫ ሕጉ መሰረት ከምርጫ ቦርድ ስልጣን አንዱ የምርጫ ክልሎችን፣ የምርጫ ጣቢያዎችን እና የክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችን ማቋቋም ነው። በዚህም መሰረት ለጠቅላላ የምርጫ ዑደት አስተማማኝነት ወሳኝ የሆኑ የመራጮች ምዝገባ፣ የዕጩዎች ምዝገባ፣ የድምጽ መስጫ ቀን አፈፃፀም እንዲሁም የድህረ- ምርጫ ሂደቶችን ያካተቱ የምርጫ ተግባራት የሚከናወኑት በእነዚሁ በሕግ በተቋቋሙ መዋቅሮች ነው። እነዚህ መዋቅሮች በመራጮች ምዝገባ፣ በእጩዎች ምዝገባ እና በድምጽ መስጫ ቀን አብዛኛውን የምርጫ ተግባራትን የማከናወን ኃላፊነት በተሰጣቸው የምርጫ አስፈፃሚዎች የተመሰረቱ ናቸው።

በኢትዮጵያ ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫን የማዘጋጀት ህጋዊ ግዴታውን ለመወጣት የምርጫ ቦርድ በምርጫ ጣቢያ፣ በምርጫ ክልል እና በክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ደረጃ ከ150,000 በላይ የምርጫ አስፈፃሚዎችን መልምሎ፣ በማሰልጠን፣ አሰማርቷል። ኅብረት ለምርጫ በስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ባደረገው ትዝብት እነዚህ የምርጫ አስፈፃሚዎች የምርጫ ሕጉ በሚያስቀምጠው መሰረት ምርጫን ለማስፈፀም የሚጠይቃቸው የቴክኒክ እና የስነምግባር አቅም ክፍተቶች እንደነበሩ ለማረጋገጥ ተችሏል። በአንዳንድ የምርጫ አስፈጻሚዎች የቴክኒክ እና የስነምግባር አቅም ማነስ ምክንያት ምርጫ ቦርድ በአንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች እና ምርጫ ክልሎች ውጤቱን ለመሰረዝ ተገዷል