Press release on the outstanding and remaining elections to take place on June 23, 2024

Press release on the outstanding and remaining elections to take place on June 23, 2024

June 22, 2024

CECOE

Addis Ababa

The Coalition of Ethiopian Civil Society Organizations for Elections (CECOE) has finalized its preparation to observe the remaining and outstanding elections in Benishangul Gumuz, Afar, Central Ethiopia, and Somali regions. 

CECOE has conducted a one-day trainings to a total of 15 Long Term Observers (LTOs)  who were drawn from  its member organizations in Assosa, Semera, Butajira, and Jigjiga cities, and deployd them to observe the pre-election environment.

CECOE also organized trainings for  the Short Term Observers(STOs) on  June 19 and 20, 2024 in Asossa, Semera, Butajira, and Jigjiga cities to equip them with the necessary skills and  knowledge to observe the electoral process on polling day.

In addition, CECOE has also organized simulation exercises for STOs  on how to report  to CECOE’s Data Center  their  observation findings  in real time using the state of art technology SMS and Apollo.

On June 23, 2024 CECOE will deploy a total of 84 stationary observers who will observe the whole election day process in the polling stations where they are assigned to observe the voting processes.

CECOE will publish a comprehensive observation report consisting of the pre-election, election Day and post-election observation findings.

ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚካሄደው ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ ከኅብረት ለምርጫ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚካሄደው ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ ከኅብረት ለምርጫ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ሰኔ 15፣ 2016 ዓ.ም

ኅብረት ለምርጫ

አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ደረጅቶች ኅብረት ለምርጫ (ኅብረት ለምርጫ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ሶማሌ ክልሎች የሚካሄደውን ቀሪ እና የድጋሚ ምርጫ ለመታዘብ ዝግጅቱን አጠናቅቋል።

ቀደም ሲል ኅብረት ለምርጫ የቅድመ ምርጫ ከባቢን ለመታዘብ በአሶሳ፣ ሰመራ፣ ቡታጅራ እና ጅግጅጋ ከሚንቀሳቀሱ አባል ድርጅቶቹ የተውጣጡ 15 የረጅም ጊዜ ታዛቢዎችን በመመልመል የአንድ ቀን ስልጠና ሰጥቶ ማስማራቱ ይታውቃል። 

በተመሳሳይም ኅብረት ለምርጫ በድምጽ መስጫ ቀን የድምጽ አስጣጥ ሂደቱን የሚታዘቡ የአጭር ግዜ ታዛቢዎች አስፈላጊው ክህሎትና እውቀት እንዲኖራቸው ሰኔ 12 እና 13 ቀን 2016 ዓ.ም በአሶሳ፣ ሰመራ፣ ቡታጅራ እና ጅግጅጋ ከተሞች 84 ታዛቢዎች የአንድ ቀን ስልጠናዎችን ሰጥቷል። ከዚህ በተጨማሪም  ለአጭር ግዜ ታዛቢወች የጽሁፍ መልዕክትን  እና የአፖሎ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የትዝብት ሪፖርታቸውን ወዲያውኑ በኅብረት ለምርጫ ፅ/ቤት ውስጥ ለተቋቋመው የመረጃ ማዕከል ሪፖርት ማድረግ የሚያስችላቸወን በተግባር የተደገፈ ስልጠና ከመስጠቱም በላይ የማስመሰል(ሲሚዩሌሽን) ልምምዶችን አዘጋጅቶላቸዋል።

ኅብረት ለምርጫ ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚካሄደው ምርጫ በአጠቃላይ 84 ተቀማጭ ታዛቢዎችን ለማስማራት አቅዷል። እነዚህ ተቀማጭ የድምጽ መስጫ ቀን ታዛቢዎች በየተመደቡባቸው የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች  ቀኑን ሙሉ የምርጫውን ሂደት እየታዘቡ የሚቆዩ ይሆናል።

በመጨረሻም ኅብረት ለምርጫ የቅድመ-ምርጫ፣ የድምጽ መስጫ ቀን እና የድህረ-ምርጫ  የትዝብት ግኝቶችን ያካተተ አጠቃላይ  ሪፖርት ይፋ የሚያደርግ መሆኑን መግለጽ ይወዳል።