የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝበ-ውሳኔ እና የወላይታ ዞን ድጋሚ ሕዝበ-ውሳኔ  አጠቃላይ የትዝብት ሪፖርት

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝበ-ውሳኔ እና የወላይታ ዞን ድጋሚ ሕዝበ-ውሳኔ አጠቃላይ የትዝብት ሪፖርት

በኢፌዲሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 47 (2) በአንቀጽ 47 (1) በተዘረዘሩት ክልሎች ውስጥ የተካተቱት ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የራሳቸውን ክልል የመመሥረት መብት ክልል የመመሥረት ጥያቄው በብሔሩ፣ በብሔረሰቡ ወይም በሕዝቡ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ተቀባይነት ማግኘቱ ሲረጋገጥ እና ጥያቄው በጽሑፍ ለክልሉ ምክር ቤት ሲቀርብ፣ ጥያቄው የቀረበለት የክልል ምክር ቤትም ጥያቄው በደረሰው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለጠየቀው ብሔር ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ ሕዝበ ውሳኔ ሲያደራጅ፣ ክልል የመመሥረት ጥያቄው ሕዝበ ውሳኔውን ባካሄደው ብሔር፣ ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ በአብላጫ ድምፅ ድጋፍ ሲያገኝ፣ እና የክልሉ ምክር ቤት የክልልነት ጥያቄ ላቀረበው ብሔር፣ ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ ሥልጣን ሲያስረክብ ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች ከተሟሉ በሕዝበ ውሳኔው የሚፈጠረው አዲስ ክልል ጥያቄ ማቅረብ ሳያስፈልገው በቀጥታ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አባል እንደሚሆን ሕገ መንግሥቱ ይደነግጋል።

ባለፉት አራት አመታት ውስጥ የደቡብ ክልል ሶስት የክልልነት ህዝበ ውሳኔዎች የተካሄዱ ሲሆን ይህ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ያካሄዱት ሕዝበ- ውሳኔ ሶስተኛው ነው። የደቡብ ክልል በ2012 ዓ.ም የሲዳማ ሕዝበ-ውሳኔን፣ በ2014 ዓ.ም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሕዝበ-ውሳኔን ማስተናገዱ የሚታወስ ነው። የስድስቱ ዞኖች እና አምስቱ ልዩ ወረዳዎች የክልልነት ጥያቄ ለፌዴሬሽን ምክርቤት የቀረበው የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝበ-ውሳኔ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል ላይ የሚነሱ የክልልነት ጥያቄዎችን መፍትሄ እንዲያፈላጉ የተሾሙ የሰላም አምባሳደሮች1 ባደረጉት አነሳሽነት እና የስድስቱ ዞኖች እና አምስቱ ልዩ ወረዳዎች ምክር ቤቶች ለፌደሬሽን ምክርቤት ባቀረቡት ማመልከቻ መሰረተ ነው። የፌደሬሽን ምክር ቤት የቀረበለትን ጥያቄ ተቀብሎ አጸድቆ ለኢትዬጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕዝበ-ውሳኔውን እንዲያስፈጽም ትዕዛዝ ማስተላለፉን ተከትሎ ሕዝበ- ውሳኔው ተግባራዊ ሆኗል።

ኅብረት ለምርጫም በደቡብ ክልል ለሶስተኛ ጊዜ የተካሄደውን የሕዝበ-ውሳኔ ወሳኝ ሂደቶችን ማለትም የቅድመ- ሕዝበ ውሳኔን፣ የሕዝበውሳኔ ምርጫ ቀንን እንዲሁም ድህረ-ሕዝበ ውሳኔን ታዝቧል። በተጨማሪም በወላይታ ዞን የተካሄደውን የደጋሚ ህዝበ ውሳኔ ሂደት ታዝቧል። በዚህም መሰረት ኅብረት ለምርጫ በትዝብት ሥራው የደረሰባቸውን አንኳር ግኝቶች በሚከተለው ክፍል ይዳስሳል።

Preliminary Statement on the Elections and Referendum Held on 30 September 2021

Preliminary Statement on the Elections and Referendum Held on 30 September 2021

It can be recalled that for the Sixth National and Regional Elections of Ethiopia, the Coalition of Ethiopian Civil Society Organizations for Election (CECOE) designed and implemented a citizen election observation project assessing imperative aspects of the voting and counting process in both June and September.

በመስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ እና ህዝበ-ውሳኔ ላይ የተደረገ የምርጫ ትዝብት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት

በመስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ እና ህዝበ-ውሳኔ ላይ የተደረገ የምርጫ ትዝብት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት

የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ሕብረት ለምርጫ በአገሪቱ የሚከናወኑ ምርጫዎች ነፃ እና ገለልተኛ እንዲሁም እንደ አካታችነት፣ ግልፅነት እና ተጠያቂነት የመሳሰሉትን አለም-አቀፍ መርሆዎችን መሰረት አድርገው መከናወናቸውን መታዘብ አንዱ ዓላማው አድርጐ መቋቋሙ ይታወቃል። ሕብረቱ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም የተደረገውን አገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ 2050 ተቀማጭ፣ እንዲሁም ከ100 በላይ ተንቀሳቃሽ ታዛቢዎችን በማሰማራት ታዝቧል።

September 30 Election Mid-Day Press Statement

September 30 Election Mid-Day Press Statement

On 21 June 2021, Ethiopia held the sixth general and regional elections in six regional states and two city administrations. However, several regional states did not cast their votes in June because of security challenges, irregularities during voter registrations as well as election day and logistics challenges.

የመስከረም 2014 ዓ.ም ምርጫ የቅድመ ምርጫ ትዝብት ሪፖርት

የመስከረም 2014 ዓ.ም ምርጫ የቅድመ ምርጫ ትዝብት ሪፖርት

ካለፈው መጋቢት 2013 ጀምሮ የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ ከስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ጋር የተያያዙ በርካታ እንቅስቃሴዎችን፤ የመራጮችን ምዝገባ እና ድህረ ምርጫ ከባቢን እንዲሁም ሰኔ 14/2013 የተካሄደውን የድምጽ መስጫ ቀን ሲታዘብ ቆይቷል፡፡