የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ በሰኔ 14፣ 2013 ዓ.ም የሚደረገውን ስድስተኛውን አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ለመታዘብ እንዲያስቸለው ከስድስት ክልሎች እንዲሁም ከሁለት የከተማ አስተዳደሮች የተመለመሉ 3,000 በላይ ታዛቢዎችን እንዳሰለጠነ የሚታወቅ ነው። ህብረቱ ታዛቢዎቹን በተለያዩ በዛሬው ቀን የሚደረገውን የድምፅ አሰጣጥ እና የቆጠራ ሂደት በሚሳተፉ ክልሎች እንዱሁም በአዲስ አበባና ድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደሮች አሰማርቷል።